የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ231 ሺህ በላይ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እየተሰራጨ ነው

By Melaku Gedif

June 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለ2017/18 ምርት ዘመን 231 ሺህ 340 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እና 5 ሺህ 292 ኩንታል ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ ነው፡፡

በክልሉ ግብርና ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ፈቃዱ ወዬሳ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልጉ የግብርና ግብዓቶችን በጊዜ አርሶ አደሮች እንዲያገኙ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች 231 ሺህ 340 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እና 5 ሺህ 292 ኩንታል ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት መታቀዱን አመልክተዋል፡፡

እስካሁን ድረስም 60 ሺህ 408  ኩንታል ዩሪያ እና 37 ሺህ 19 ኩንታል ዳፕ በድምሩ 97 ሺህ 427 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልሉ መግባቱን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም 24 ሺህ 244 ኩንታል ዩሪያ እና 14 ሺህ 858 ኩንታል ዳፕ ለአርሶ አደሮች መሰራጨቱን ነው ያስረዱት፡፡

በሌላ በኩል 4 ሺህ 589 ኩንታል ምርጥ ዘር ወደ ክልሉ የገባ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ 3 ሺህ 37 ኩንታል ተሰራጭቷል ብለዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!