የሀገር ውስጥ ዜና

የስሎቬኒያ ፕሬዚዳንት ናታሻ ፒርስ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ

By Adimasu Aragawu

June 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የስሎቬኒያ ፕሬዚዳንት ናታሻ ፒርስ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

ፕሬዚዳንቷ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባታቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ፕሬዚዳንቷን ተቀብለው የዓድዋ ድል መታሰቢያን አስጎብኝተዋል።

ፕሬዚዳንቷ በቆይታቸው ከከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በግዛቸው ግርማዬ