አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሕንድ ሃይድራባድ በተዘጋጀው የ’ሚስ ወርልድ’ ዓለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር 2ኛ የወጣችው ሞዴል ሀሴት ደረጀ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል፡፡
ለ72ኛ ጊዜ በተደረገው የቁንጅና ውድድር የ108 ሀገራት ተወዳዳሪዎች የተሳተፉ ሲሆን÷ ሀሴት በዓለም አቀፍ ደረጃ 2ኛ ከአፍሪካ ደግሞ ቀዳሚ በመሆን ነው ያጠናቀቀችው፡፡
ሀሴት ደረጀ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታዎች ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) እና ነፊሳ አልማሃዲ አቀባበል አድርገውላታል፡፡
በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ሀሴት ደረጀ የኢትዮጵያ ባህል አምባሳደር በመሆን መሾሟን የሚገልጽ የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷታል፡፡
በምንተስኖት ሙሉጌታ