የሀገር ውስጥ ዜና

የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየተከበረ ነው

By Abiy Getahun

June 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 446ኛዉ የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ከተሞች እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ በተለያዩ ከተሞች እና ወረዳዎች በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።

በክልሉ በተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በጋራ በመሰባሰብ ሶላትን ጨምሮ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በዓሉን በድምቀት እያከበሩ ይገኛሉ፡፡