ስፓርት

ራፊንሀ -የስፔን ላሊጋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች

By ዮሐንስ ደርበው

June 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዚላዊው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር ተጫዋች ራፊንሀ የ2024/25 የውድድር ዓመት የስፔን ላሊጋ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል፡፡

ራፊንሀ በውድድር ዘመኑ ለባርሴሎና 36 የላሊጋ ጨዋታዎችን በማድረግ 18 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡

እንዲሁም ዘጠኝ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አማቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡

ባርሴሎና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሀንሲ ፍሊክ እየተመራ የስፔን ላሊጋ ዋንጫን ሲያሳካ የራፊንሀ ሚና የጎላ ነው፡፡

አሸናፊውን ራፊንሀን ጨምሮ ላሚን ያማል፣ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ፣ ቪኒሸስ ጁኒየር፣ ጁድ ቤሊንግሀም፣ ኪሊያን ምባፔ፣ ሳንሴት፣ ኢስኮ እና ፔድሪ ለዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት በእጩነት ቀርበው ነበር፡፡

የላሊጋው አሸናፊ ባርሴሎና በምርጥ ተጫዋች እጩዎች ዝርዝር አራት በማሳለፍ ቀዳሚ ነው፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ