የሀገር ውስጥ ዜና

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ መሰረታዊ የኮማንዶ ሰልጣኞችን እያስመረቀ ነው

By Yonas Getnet

June 07, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ በብላቴ ማሰልጠኛ ማዕከል በ43ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን መሰረታዊ የኮማንዶ ሰልጣኞች እያስመረቀ ነው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ወታደራዊ መኮንኖች ተገኝተዋል።

ተመራቂ ወታደሮቹ በተግባር ለአንድ ዓመት ያህል መሰረታዊ የውትድርና ሳይንስ እና የኮማንዶ ሥልጠና ሒደትን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ተመራቂዎች ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርዒቶችን አቅርበዋል።

በሃይለማርያም ተገኝ