አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ እና ኢራን በሳተላይት ልማት እና በስፔስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
በሩሲያ የኢራን አምባሳደር ካዚም ጃላሊ ከሩሲያ የጠፈር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዲሜትሪ ባካኖቭ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ሀገራቱ የሳተላይት ዲዛይኖችን በትብብር ለመቅረጽና ለማምረት እንዲሁም የጠፈር ምርምር መሰረተ ልማቶችን መዘርጋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም ዘመናዊ የህዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂዎችን በጋራ ማምረት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በሳተላይት ልማት እና በስፔስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ የልምምድ ልውውጥ ለማድረግ እና በቅንጅት ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
ዓለም አቀፋዊ ሰላም እና ደህንነትን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሀገራቱ በትብብር እንደሚሰሩ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ሞስኮ እና ቴህራን ከሳተላይት ልማት ባለፈ በንግድ እና ኢነርጂ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ