የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም የቁንጅና ውድድር 2ኛ ለወጣችው ሀሴት ደረጀ ሽልማት አበረከቱ

By Melaku Gedif

June 07, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሕንድ ሃይድራባድ በተዘጋጀው የ’ሚስ ወርልድ’ ዓለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር 2ኛ ለወጣችው ሞዴል ሀሴት ደረጀ የወርቅ ሽልማት አበርክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ “ሀገር እና ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ ከተማ አቀፍ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ 72ኛው የዓለም ቁንጅና ውድድር ላይ 2ኛ በመውጣት የኢትዮጵያ ስም በዓለም መድረክ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ላደረገችው ሀሴት ደረጀ የወርቅ ሽልማት አበርክተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ሀሴት በዓለም አቀፍ መድረክ ያሳየችው ብቃት ለበርካታ ወጣቶች አርአያ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

ሀሴት ደረጀ የአዲስ አበባ ቱሪዝም እና ባህል አምባሳደር ሆና እድትሰራ ተልእኮ የተሰጣት መሆኑንም የከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ሚኤሳ ኤሌማ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በዓለም የቁንጅና ውድድር 2ኛ የወጣችው ሀሴት ደረጀ ከተማ አስተዳደሩ ላበረከተላት ሽልማት ምስጋና አቅርባለች፡፡

በመላኩ ገድፍ