የሀገር ውስጥ ዜና

ከ23 ሚሊየን በላይ ዜጎች በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሳተፋሉ

By ዮሐንስ ደርበው

June 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ23 ሚሊየን በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ አለ፡፡

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ 14 መርሐ ግብሮች እንዳሉት በሚኒስቴሩ የወጣቶች ብሔራዊ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስፋፊያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዐቢይ ኃ/መለኮት ተናግረዋል።

የዳበረ የመደጋገፍ ዕሴትን ለማሳደግ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የላቀ ሚና እንዳለው አስረድተዋል፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎን በማሳደግ አሠራሩን መዋቅራዊ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በስንታየሁ አበበ