የሀገር ውስጥ ዜና

ለአትክልትና ፍራፍሬ የተሰጠው ትኩረት ለምጣኔ ሀብት ዕድገት ከፍተኛ ሚና አለው

By Yonas Getnet

June 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለአትክልትና ፍራፍሬ የተሰጠው ትኩረት ለሀገራዊ ምጣኔ ሀብት ዕድገት ከፍተኛ ሚና አለው አሉ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪዎች፡፡

የዘርፉ ተመራማሪ አቡሌ መሐሪ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የወጪ ንግዱን ለማሳደግ እና የዋጋ ግሽበትን ለማስተካከል ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

በአረንጓዴ ዐሻራ ለአትክልትና ፍራፍሬ የተሰጠው ትኩረት ቀጣይነት ባለው መልኩ ሊሠራበት እንደሚገባ ያመላከቱት ደግሞ ሌላኛው የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ አረጋ ሹመቴ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

በየዓመቱ የሚተከሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞች የኢንዱስትሪዎችን ጥሬ ዕቃ ከማሟላት ባሻገር፤ በኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት እድገት የጎላ ሚና እንዳላቸው ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን