የሀገር ውስጥ ዜና

ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማምጣት የመንግሥት አገልግሎት ዘርፉ ከፍተኛ ሚና አለው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

By Abiy Getahun

June 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማምጣት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፉ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡

ዛሬ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር ዐቢይ ኮሚቴ አምስተኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂደናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መረጃ ገልጸዋል።

በውይይታችን በመጀመሪያ ዙር ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የገቡ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ እና በሁለተኛው ዙር ለመግባት ዝግጅት ያጠናቀቁ ተቋማትን ቅድመ ዝግጅትን ተመልክተናል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም የሁሉም ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች መሶብን ለማስጀመር እያከናወኑ የሚገኙትን የቅድመ ዝግጅት እንቅስቃሴ ሪፖርትን ገምግመናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመጀመሪያ ዙር ወደ መሶብ የገቡ ተቋማት በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ታይቷል ብለዋል።

በሁለተኛ ዙር ወደ መሶብ የሚገቡ ተቋማት እና በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የሚከናወኑ ተግባራት እንዴት መስራት እንዳለባቸዉ እና ለተግባራዊ እንቅስቃሴያቸው አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቁመዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!