የሀገር ውስጥ ዜና

የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ እየተሰራ ነው

By Adimasu Aragawu

June 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የክልሎችን አቅም በማጠናከር የክረምት ጎርፍ አደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ እየሰራሁ ነው አለ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሽፈራሁ ተክለማርያም (ዶ/ር) ከክልሎች ጋር ለጎርፍ አደጋ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ስራ በቅንጅት መሰራቱን ገልጸዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባለፈው ዓመት በጎርፍና መሬት ናዳ የተፈናቀሉ ዜጎችን ዳግም የማቋቋም ስራ ባለፉት 10 ወራት ከመስራት በተጨማሪ የቅድመ መከላከል ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ጋንታ ጋማ ተናግረዋል።

ቀሪዎቹን የጎርፍና የመሬት ናዳ ተጎጂዎች የሰኔ ወር ሳይጠናቀቅ ወደ ሌላ ቦታ የማስፈር ስራ መከናወኑ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

የአማራ ክልል በበጋ ወራት 145 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ የጎርፍ ቅድመ መከላከል ስራ መከናውኑን የገለጹት ደግሞ በክልሉ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ዘውዱ ናቸው።

በክልሉ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ 33 ወረዳዎችን በመለየት ህብረተሰቡን ያሳተፈ ቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራቱንም ጠቁመዋል።

በእዮናዳብ አንዷለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!