ፋና ስብስብ

5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ሰኔ 7 ይጀመራል

By Adimasu Aragawu

June 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የፊታችን ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ይጀመራል፡፡

በውድድሩ የምዕራፍ 17፣ 18 እና 19 አሸናፊዎች እንዲሁም ምርጥ አራት ተሰናባቾች ዳግም ተመልሰው በአጠቃላይ 16 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ፡፡

ለአሸናፊዎች አጠቃላይ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን÷ ዋንጫ እና የአዲስ ወጥ ሙዚቃ ሽልማትም ተዘጋጅቷል፡፡

የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት በሚያደርገው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖራል፡፡

በ13ኛው ሳምንት አራት ምርጥ ተወዳዳሪዎች ለፍጻሜው የሚፋለሙ ሲሆን÷ 5ኛው የፋና ላምሮት አሸናፊዎች አሸናፊ ኮከብ ይለይበታል።

ውድድሩ በየሳምንቱ በተለያየ ሙያ ውስጥ ባሉ ተጋባዥ ዳኞች ጭምር ይደምቃል።

የመጀመሪያዋ የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ መቅደስ ግርማ ስትሆን÷ አህመድ ሁሴን፣ ያለምወርቅ ጀምበሩ እና ባምላክ ቢያድግልኝ ደግሞ በቅደም ተከተል 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛውን ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም የሚጀመረውን 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ደማቅ ውድድር በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሁሉም አማራጮች በቀጥታ ሥርጭት ይተላለፋል። ይጠብቁን፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!