አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጣና ሐይቅ የመዝናኛና የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ወደ ሀገር የገባችው ጣና ነሽ ፪ ጀልባ አዳማ ከተማ ደርሳለች።
ጀልባዋ በዛሬው ዕለት አዳማ ከተማ ስትደርስ የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት አቀባበል አድርገዋል።
እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴን ጨምሮ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የሥራ ኃላፊዎች በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጀልባዋን ለማሳለፍ በመንገድ ላይ ያሉ የኤሌክትሪክ ገመዶችን በማንሳት እንዲሁም የሚቋረጡ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን በፍጥነት በመመለስ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።
በተጨማሪም የከተማው አስተዳደር የትራፊክ መብራቶችን በማንሳት ጭምር ጀልባዋ በምታልፍባቸው መንገዶች አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ላይ ነው።
ጣና ነሽ ፪ ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት ጀልባ 38 ሜትር ርዝመት ያላት ሲሆን፥ በአንድ ግዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም እንዳላት የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መረጃ ያመለክታል።
በኃይለማርያም ተገኝ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!