የሀገር ውስጥ ዜና

ወጣቶች የተለያዩ ጉዳዮችን ከሀገር ጥቅም አንፃር እንዲመለከቱ ጥሪ ቀረበ

By Adimasu Aragawu

June 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወጣቶች የተለያዩ ጉዳዮችን ከሀገር ጥቅም አንፃር በማየት ተሳትፏቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በከተማ ደረጃ የወጣቶች የማጠቃለያ ውይይት መድረክ ተካሂዷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት÷ መዲናዋን ለወጣቶች ምቹ ለማድረግ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውንና የተሰራውን ስራ በኃላፊነት መጠቀም እና በባለቤትነት መጠበቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሀገር ተስፋ እና ኩራት የሆነው ወጣት ለሀገር ጠቃሚ በሆኑ ስራዎች ላይ ወደኋላ ሳይል በትኩረት መስራት እንዳለበት አንስተው÷ የተለያዩ ጉዳዮችን ከሀገር ጥቅም አንፃር በማየት ጉልህ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸውም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ህልም ብልፅግና መሆኑን ገልጸው÷ ወጣቱ ይህንን በመረዳት ህልሟን ለማሳካት በአብሮነት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

የሚፈጠሩ የስራ ዕድሎችን በአግባቡ በመጠቀም ለመለወጥ መስራት ሌላው ከወጣቱ ትውልድ የሚጠበቅ ጉዳይ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው÷ እንደ ሀገር ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ባህል ያደረገ ወጣት ለማፍራት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህም ባለፉት ጊዜያት በመዲናዋ ከ1 ሺህ 400 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን ገልጸው÷ የማዘውተሪያ ስፍራ ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመልክተዋል።

በተለያዩ ጊዜያት ውድድሮች ሲደረጉ በስፖርታዊ ጨዋነት ውድድሩ እንዲጠናቀቅ ከማድረግ አንፃር የወጣቱ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ይህንንም በኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል።

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!