አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል 12 ሺህ 662 ተማሪዎች በወረቀት እና በኦንላይን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ የሚያስችላቸውን ዝግጅት አድርገዋል አለ የክልሉ ትምህርት ቢሮ፡፡
በዚሁ መሠረት በጋምቤላ እና ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናው በተያዘለት መርሐ ግብር በወረቀት እንደሚሰጥ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ፖክ ካዊች ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ 990 የማኅበራዊ እና ተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎች በኦንላይን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ እንደሚወስዱ አስረድተዋል፡፡
በወረቀት እና በኦንላይን ለሚሰጡት ፈተናዎችም ለተማሪዎች የልምምድና የሞዴል ፈተናዎች መሰጠታቸውን ነው የገለጹት፡፡
በዮሐንስ ደርበው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!