አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ ባለሙያዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን እየጎበኙ ነው። ባለሙያዎቹ በጉራጌ ዞን የግቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ ጨምሮ በዞኑ የሚገኙ ባህላዊ መስህቦችን ተመልክተዋል። የግቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ በክልሉ የሚገኝ ብቸኛ ፓርክ ሲሆን÷ በውስጡ የያዛቸው መልከዓ ምድራዊ እና ተፈጥሯዊ መስህቦች በቱሪስቶች ተመራጭ ያደርገዋል። ይሁን እንጂ ፓርኩ እና መሰል መስህቦች መዳረሻ የመሆን አቅማቸው ከፍተኛ ቢሆንም የማስተዋወቅ ስራ ባለመሰራቱ ተገቢውን ጎብኚ ቁጥር እያስተናገዱ አለመሆናቸው ተገልጿል።
እንዲሁም በቀቤና ልዩ ወረዳ የቀቤና ባህል ማዕከልን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎቹ ጎብኝተዋል። በቱሪዝም ሚኒስቴር የተመራው የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ቡድን ጉብኝት መስህቦቹን ለማስተዋወቅ ያለመ እንደሆነም ተጠቁሟል። በክልሉ እየተካሄደ የሚገኘው የመስህብ ስፍራዎች ጉብኝት ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል።
በሚኪያስ ዓለሙ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!