አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
ቀን 9 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሀቢብ ከማል በፍጹም ቅጣት ምት በ45ኛው ደቂቃ ቀዳሚውን ግብ ለድሬዳዋ ከተማ ሲያስቆጥር÷ ሲዳማ ቡናን አቻ ያደረጋትን ግብ ሀብታሙ ታደሰ በ54ኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችሏል።
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ወላይታ ድቻ እና ባህር ዳር ከተማ ይገናኛሉ።