አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከምንጊዜም ምርጥ ኢትዮጵያውያን የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ሙሉጌታ ከበደ ቀብር ሥነሥርዓት ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል።
ዛሬ ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የአስክሬን ሽኝት መርሐ ግብር ከተደረገ በኋላ ቤተሰቦቹ፣ የእግር ኳስ አፍቃሪያን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና የክለብ ተወካዮች በተገኙበት ነው ሥርዓተ ቀብሩ የተፈጸመው።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮከብና የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ሙሉጌታ ከበደ ባጋጠመው ህመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡
ሙሉጌታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ለበርካታ ዓመታት በድንቅ ብቃት ተጫውቶ አሳልፏል፡፡
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ በነበረው ቆይታ አምበል ሆኖም መጫወት የቻለ ድንቅ ተጫዋች ነበር።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!