አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ወላይታ ድቻን 4 ለ0 አሸንፏል።
ምሽት 12 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ወንድወሰን በለጠ በሁለተኛው አጋማሽ ለባህር ዳር ከተማ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።
በተጨማሪም ቀሪዋን አንድ ግብ ፍፁም አለሙ ከእረፍት በፊት አስቆጥሯል።
በዚሁም ባህር ዳር ከተማ ወላይታ ድቻን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ቀደም ብሎ ቀን 9 ሰዓት በተካሄደው የሊጉ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ ተጫውተው 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!