የሀገር ውስጥ ዜና

ልማትና ዕድገትን ለማፋጠን አመራሩ ሚናውን ሊያጠናክር ይገባል – አቶ አረጋ ከበደ

By Melaku Gedif

June 13, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ልማትና እድገትን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት አመራሩ ሚናውን ይበልጥ አጠናክሮ ሊወጣ ይገባል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ።

“አርቆ ማየት አርቆ መስራት” በሚል መሪ ሃሳብ የአማራ ክልል አሻጋሪ ዕድገትና የልማት ዕቅድ ዙሪያ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀው የስልጠና መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተጀምሯል።

ርዕሰ መስተዳደሩ በማስጀመሪያ ሥነ ሥርአቱ ላይ እንደገለፁት፤ በክልሉ ከድህነት ለመላቀቅ የሚያስችል የ25 ዓመት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቷል።

ከፍኖተ ካርታው የተቀዳና ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ የሚተገበር የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ መዘጋጀቱን ገልጸው፤ ዕቅዱን በማሳካት የክልሉን ልማትና ዕድገት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት አመራሩ ሚናውን ይበልጥ ሊያጠናክር ይገባል ብለዋል።

የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በየጊዜው የሚከሰቱ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮች ክልሉ ባለው የመልማት ፀጋ ልክ ወደፊት እንዳይራመድ አድርገውታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከችግሩ በዘላቂነት ለመላቀቅ የሚያስችል ዕቅድ መዘጋጀቱን ጠቅሰው፤ አመራሩ ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል አሻጋሪ የልማት ዕቅዱ እንዲሳካ የላቀ ሚናውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ዛሬ የተጀመረው የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እስከ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ይቀጥላል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!