አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በሚገባ ለመጠቀም የኢኖቬሽንና የፈጠራ ሥራዎችን ማበረታታት ይገባል አሉ የአፍሪካሊክስ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቅጣው (ፕ/ር) ፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኢትዮጵያሊክስ ዓለም አቀፍ ጉባዔ “ለኢኖቬሽን ምቹ ከባቢን መፍጠር ለዕውቀት ኢኮኖሚ ሽግግር እና ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው።
ዳንኤል ቅጣው (ፕ/ር) በዚህ ወቅት ÷ ግሎባሊክስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች እና ፖሊሲ አውጪዎችን የማገናኘት ሥራ እንደሚሰራ አንስተዋል፡፡
ዓለም አቀፋዊ የኢኖቬሽን ሥራዎች በኢትዮጵያ አውድ ተቀይረው የሚተገበሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የተፈጥሮ ሃብት፣ ባህልና እሴት ያላት ሀገር መሆኗን አውስተው÷ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችን ማሳደግና ማበረታታት እንደሚደባ ተናግረዋል፡፡
የኢኖቬሽን ሥራዎች ለሕይወት መሻሻል ትልቅ ሚና አላቸው፤ በአንጻሩ ጉዳት የሚያደርሱ የኢኖቬሽን ሥራዎች መኖራቸውን ያነሱት ደግሞ የግሎባሊክስ ፕሬዚዳንት ኤሪካ ካራሜር ምቡላ (ፕ/ር) ናቸው።
በኢኖቬሽን ዘርፉ ላይ ያለው እንቅስቃሴን በተገቢው መንገድ በመምራት ማሳደግ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያሊክስ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ እድገት ዙሪያ ትብብር ለመፍጠር ያለመ ፋውንዴሽን ነው።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!