አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የምትበለፅገው የራሳችንን የሰው ሀይልና የተፈጥሮ ሀብት አቀናጅቶ በማልማት ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
‘ብሩህ አዕምሮዎች፣ በክህሎት የበቁ ዜጎች’ በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀውን የቴክኒክና ሙያ ቴክኖሎጂ ዐውደ ርዕይ በይፋ ተከፍቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለሀገር ብልፅግና ያላቸውን የማይተካ ሚና በአግባቡ በመገንዘብ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት አመርቂ ውጤት መመዝገቡ ተመላክቷል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ እየተከነወኑ ባሉ የልማት ስራዎች ውስጥ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የእጅ ሥራ ውጤት የሆኑ የተለያዩ ተኪ እና ጥራት ያላቸዉ ግብዓቶችን ከማቅረብ ጀምሮ የሰለጠነ የሰዉ ሀይል በማፍራት በበርካታ ሥራዎች ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ ይገኛሉ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዐውደ ርዕይ ላይ የቀረቡ የቴክኖሎጂ ሥራዎች ላይ የበኩላቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትን ምስጋና አቅርበዋል።
ዐውደ ርዕዩ ላይ የቀረቡ ቴክኖሎጂዎች የሀገራችን ብልጽግና የሚሳካው በቴክኖሎጂ አመንጪ ኢትዮጵያውያን ለመሆኑ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!