የሀገር ውስጥ ዜና

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 2 ሺህ 500 ቤቶችን ለመገንባት አቅደናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By Abiy Getahun

June 14, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 2 ሺህ 500 ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ይዘናል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

የከተማ አስተዳደሩ የዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህል ሆኖ መቀጠል ያለበት መልካም ተግባር ነው።

በለውጡ ዓመታት በከተማዋ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችንና ባለሃብቶችን በማስተባበር የበጎ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን ጠቅሰው፤ ዘንድሮም በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት እንደሚፈጸሙ አረጋግጠዋል።

18 የተለያዩ በጎ ፈቃድ ተግባሮችን ለመተግበር መታቀዱን ጠቅሰው፤ በመርሐ ግብሩ 2 ሺህ 500 ቤቶችን በ90 ቀናት ለመገንባት መታቀዱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም 500 ሺህ የሚሆኑ ለከተማዋ ነዋሪዎች በድግግሞሽ ማዕድ የማጋራት ዕቅድ መያዙንም አመልክተዋል።

በነፃነት ፀጋይ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!