አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሪያል ማድሪድ የስፔናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ራውል አሴንሲዮ ከክለቡ ጋር ያለውን ውል እስከ የፈረንጆቹ 2031 ድረስ አራዝሟል፡፡
የ22 ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ራውል አሴንሲዮ በሪያል ማድሪድ እስከ 2029 የሚያቆይ ኮንትራት ቢኖረውም ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለመቆየት ተስማምቷል፡፡
ሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ራውል አሴንሲዮ አዲስ ኮንትራት ላይ አንድ ቢሊየን ዩሮ የውል ማፍረሻ ማስቀመጡን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
ራውል አሴንሲዮ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በስፔን ላሊጋ እና አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር 33 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ለሪያል ማድሪድ ግልጋሎት መስጠት የቻለ ሲሆን ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!