አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የቱሪዝም ሀብቶችን የማልማት፣ የመጠበቅና የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ ነው።
የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን እየጎበኙ ይገኛል።
የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኑር ከድር እንደገለጹት፤ በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ማልማት ትኩረት ተሰጥቶታል።
የቱሪስት መስህቦችን ማልማት እንዲቻል እና ተደራሽነታቸውን ለማሳደግ ኢንቨስትመንት ምቹነትን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸው፤ የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለማስፋት የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህንን በመገንዘብም የግሉ ዘርፍ ቱሪዝምን ሊደግፉ በሚችሉ ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ እየተሰራ እንደሆነ አመልክተዋል።
የቱሪዝም ሀብቶቹን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የማልማት፣ የመጠበቅ እና የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ ነው ያሉት ምክትል ኃላፊው፤ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጉብኝትም መዳረሻዎችን የማስተዋወቅ አካል መሆኑን ገልጸዋል።
ባለሙያዎቹ በክልሉ የሚገኙ ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ባህላዊ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን እየጎበኙ ሲሆን፤ በጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ እና ሀዲያ ዞኖች የሚገኙ ስፍራዎችን ተመልክተዋል።
የግቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ፣ ስልጤ አባያ ሐይቅ፣ የአንገሪ ቤተመንግሥት፣ አርቶ ፍልውሃ እና መጨፈር ሀይቅ ከጎበኟቸው የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
በሚኪያስ ዓለሙ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!