የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኮሮናን ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለዞንና ልዩ ወረዳዎች የፓርቲው ፅ/ቤቶች አበረከተ

By Feven Bishaw

August 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኮሮናን ለመከላከል የሚረዱ የንጽህና መጠበቂያ እና የህክምና ቁሳቁሶችን ለዞንና ልዩ ወረዳዎች የፓርቲው ፅህፈት ቤቶች አበረከተ፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው በክልሉ 16 ዞኖችና 7 ልዩ ወረዳዎች የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ናቸው ተብሏል፡፡