ዓለምአቀፋዊ ዜና

በህንድ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ የሟቾች ቁጥር 270 ደረሰ

By Abiy Getahun

June 14, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በህንድ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ የሟቾች ቁጥር 270 ደርሷል፡፡

ከተከሰከሰ ሶስተኛ ቀኑን የያዘው አውሮፕላኑ የ270 ሰዎችን ሕይወት ሲቀጥፍ አንድ ተሳፋሪ በህይወት መትረፉ አይዘነጋም፡፡

በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት መካከል 29 ሰዎች አደጋው በደረሰበት ስፍራ የነበሩ መሆናቸውን ገልፍ ቱዴይ ዘግቧል።

በአህመዳባድ በሚገኘው የሲቪል ሆስፒታል ዶ/ር ዳቫል ጋሜቲ ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደተናገሩት፤ ተቋሙ 270 አስከሬኖችን አግኝቷል።

ከአውሮፕላኑ 242 መንገደኞች መካከል በህይወት የተረፈው ብቸኛው ሰው የህክምና ክትትል ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

በመቶዎች የሚቆጠሩ የአደጋው ተጎጂ ቤተሰቦች በሆስፒታሉ ውስጥ የዲኤንኤ ናሙና የሰጡ ቢሆንም የዲኤንኤውን ውጤት ለማወቅ እስከ 72 ሰዓታት እንደሚፈጅ ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ቦይንግ 787- 8 የሚል ስያሜ ያለው አውሮፕላን በሰሜን ምዕራብ ህንድ ከሚገኘው አህመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ለንደን በረራ በጀመረ በሴኮንዶች ውስጥ የመከስከስ አደጋ እንዳጋጠመው ይታወሳል።

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!