አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ምክትል ጠቅላይ ማኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በባህር ዳር ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።
በጉብኝቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) እና ሌሎች የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
ባህርዳር ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ÷ በዓባይ ወንዝ ላይ የተገነባውን ድልድይ እና የጣና ሐይቅ ዙሪያ እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ተመልክተዋል።
በባህርዳር የኮሪደር ልማት ሥራ በመሥራት የጣና ሐይቅን ከከተማዋ ጋር የማስተሳሰር ሥራ እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህም የከተማዋ ነዋሪዎች በውስን ስፍራዎች ብቻ የነበራቸውን ትስስር በማስፋት በሐይቁ አምስት አቅጣጫዎች በተሰራው ልማት ሐይቁ ለከተማዋ ያለውን አበርክቶ ለማስፋት እየተሰራ ነው።
በባህርዳር ከተማ የተሰራው ዘመናዊ ድልድይ በከተማዋ ያለውን የትራፊክ እንቅስቃሴ ከማቀላጠፍ ባለፈ ለቱሪዝም እና መሰል የከተማዋ ልማቶች ልዩ አበርክቶ አለው።
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!