ቢዝነስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀይድራባድ በረራ ጀመረ

By Adimasu Aragawu

June 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በህንድ አምስተኛ መዳረሻውን የሀይድራባድ በረራ አስጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው÷ አየር መንገዱ በዛሬው ዕለት ያስጀመረው የሀይድራባድ ቀጥታ በረራ የሁለቱን ሀገራት ትስስር የሚያሳድግ መሆኑን ገልጸዋል።

አየር መንገዱ በዓለም ከ140 በላይ መዳረሻዎች እንዳሉት አስታውሰው÷ ከአዲስ አበባ ሀይድራባድ ቀጥታ በረራ መጀመር በሀይድራባድ ላሉ በርካታ አፍሪካዊያን አማራጭ ትራንስፖርት እንደሚሆን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በካርጎ ቀደም ሲል ወደ ከተማዋ መብረር እንደጀመረና በመንገደኞች የመጀመሪያው እንደሆነ ገልጸው÷ በረራው በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ላይ የራሱን ድርሻ የሚጫወት ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ሺሪ አኒል ኩመር በበኩላቸው÷ ሀይድራባድ ለህንድ ወሳኝ ከሚባሉ ከተሞች አንዷ በመሆኗ በረራው ለሀገራቱ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በረራው ሀይድራባድን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኝ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ከተሞችንም በማስተሳሰር በትራንስፖርት ዘርፉ ትልቅ ድርሻ ይጫወታል ሲሉም ገልጸዋል።

በታሪኩ ለገሰ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!