የጥበብ ባለሙያዎች በችግር ጊዜ የሀገርን ጥቅም ሊያስቀድሙ ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በችግር ጊዜ ከግል ጥቅም ይልቅ ለሀገር ጥቅም የተሳተፉ የጥበብ ባለሙያዎች ስማቸው ምንጊዜም በወርቅ አሻራ ተጽፎ ይኖራል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ የጥበቡ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት÷ የኪነ ጥብብ ባለሙያዎች በየትኛውም ሁኔታ ለሀገር ጥቅም መከበር ቁርጠኛ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡
ባለሙያዎች በተከናወኑ የልማት ሥራዎች ላይ ሙዚቃ፣ ፊልም፣ ኮንሰርትና ሌሎች የጥበብ ክዋኔዎችን በመስራት ለማሕበረሰቡ ማሳየት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ኢትዮጵየ በኢኮኖሚ ፈጣን እድገት እያሳየች መሆኑን አንስተው ÷ የኪነ ጥበብ ባለሙዎችም የኢኮኖሚ እድገቱን የዋጀ ዝግጁነት ሊኖራቸው ይገባል ነው ያሉት፡፡
በችግር ጊዜ ከግል ጥቅም ይልቅ ለሀገር ጥቅም የተሳተፉ የጥበብ ባለሙያዎች ስማቸው ምንጊዜም በወርቅ አሻራ ተጽፎ እንደሚኖር አንስተዋል፡፡
በችግር ጊዜ ሀገራቸውን ለከዱት ይቅርታ አድርገናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ ኢትዮጵያን ክዶ ከመጣው ጋር በጥቅም ተሳስሮ ሃብታም ከመሆን ቢቀር ይሻላል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ኪነ ጥበብ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ብልጽግና የማይተካ ሚና እንዳለው ገልጸው ÷ ለሀገር አንድነትና ግንባታ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፏቸው የመደመር እና የመደመር ትውልድ መጽሃፎች ላይ ኪነ ጥበብ ለአንድ ሀገር እድገት ያለው ድርሻ በግልጽ መቀመጡን አስታውሰዋል።
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!