አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የወንዝነት ባህሪያቸውን ለቀው የነበሩትን የመዲናዋ ወንዞች ከብክለት ለመከላከል 44 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት እየተከናወነ ነው አለ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ዲዳ ድሪባ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በባለስልጣኑ በተደረጉ ጥናቶች ወንዞቹ የተፈጥሮ መልካቸውን ለቀው ለከፍተኛ ብክለት ተጋልጠዋል፡፡
በዚህም ወንዞችን ከብክለት ለመከላከል 44 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት እየተከናወነ እንደሆነ ተናግረዋል።
የወንዝ ዳርቻ ልማቱ የህዝብ መዝናኛዎች፣ መጸዳጃ ቤቶች፣ የልጆች መጫወቻዎች፣ የአትሌቶች መለማመጃዎችን እና ፓርኮችን አካቶ እየተገነባ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ንጋቱ ዳኛቸው በበኩላቸው÷ ወንዞችን ከብክለት ለመጠበቅ የወንዞች ልማትና ብክለት መከላከል ደንብ ወደ ስራ ገብቷል ብለዋል፡፡
ደንቡ ወደ ወንዝ ዳርቻ ልማቱ በካይ ነገሮችን የለቀቁ ግለሰቦች እና ተቋማት ከ2 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ እንደሚቀጡ ተደንግጓልም ነው ያሉት።
በመሳፍንት እያዩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!