አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በክልሉ 90 የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ናቸው አለ።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል ፕሮጀክቶቹ በ”አንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት” በሚል ኢኒሼቲቭ እየተሰሩ መሆናቸውን ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
በዚህም 18 የፐብሊክ ፋርማሲ፣ 10 የጤና ተቋማት፣ 10 የትምህርት ቤት ግንባታዎች፣ 10 የከተማ መብራት ዝርጋታዎች፣ ሰባት የውሃ መስመር ዝርጋታዎች እና ሌሎች ተመሳሳይ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡
የፕሮጀክቶቹ ግንባታ በ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር መነሻ ወጪ እየተከናወኑ እንደሆነ ገልጸው÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓመቱ የመጀመሪያ ዙር የአመራር ስልጠና መድረክ ላይ በሰጡት አቅጣጫ መሠረት እየተሰሩ ስለመሆናቸውም አመልክተዋል።
ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ስንታየሁ ገልጸዋል፡፡
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!