የሀገር ውስጥ ዜና

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በሁለት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

By Hailemaryam Tegegn

June 17, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወንጀል የተገኘን ንብረት ሕጋዊ ማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበውን የማሻሻያ አዋጅ አፅድቋል፡፡

የማሻሻያ አዋጁ በሦስት ተቃውሞ እና በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 37ኛ መደበኛ ስብሰባ የተወያየበት ሌላኛው ጉዳይ የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅ ሲሆን፥ ረቂቅ አዋጁን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

በመራኦል ከድር