አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ሀገር አቀፍ የስፖርት ጨዋታዎች የነገ የሀገር ተረካቢ ወጣቶች ሀገራቸውንና ባሕላቸውን እንዲያውቁ ዕድል የሚፈጠርበት መድረክ ነው አሉ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ስፖርት ለኅብረ ኢትዮጵያ አርበኝነት” በሚል መሪ ሃሳብ በጅማ ከተማ የተዘጋጀውን 6ኛው የመላው ኢትዮጵያ ስፖርት ጨዋታ አስጀምረዋል።
በዚህ ወቅትም መሪ ሃሳቡን በትክክል በምትገልጸው እና ለዘመናት የኅብረ ብሔራዊነት መናኸሪያ በሆነችው በአባ ጅፋር ሀገር ጅማ የተጀመረው የስፖርት ጨዋታ ወጣት ስፖርተኞች አስፈላጊ የሕይወት ክኅሎቶችን፣ አካታችነትን፣ ፍትሐዊነትን፣ የቡድን ሥራን እና ኃላፊነትን እንዲያዳብሩ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።
ስፖርት የነገዋን ኢትዮጵያ ዜጎች መፍጠሪያችን ነው፤ የነቃና የበቃ ትውልድ የምናፈራበት መስካችን ነው ያሉት አቶ ተመስገን ÷ ለዚህም በየአካባቢው የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በአነስተኛ፣ በመካከለኛ እና በከፍተኛ ደረጃ እየገነባን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል።
ለአብነትም ዛሬ የተጀመረውና በተለያዩ ምክንያቶች ለዘጠኝ ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ጉልህ ማሳያ መሆኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
በስፖርታዊ ጨዋታ ለተሳተፉ የክልልና የከተማ አስተደዳሮች፣ የውድድር አዘጋጅ ለሆነው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እንዲሁም ለኦሮሚያ ክልልና ለጅማ ከተማ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!