አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከታሪካዊው ዓድዋ ድል መታሰቢያ ጋር ተሰናስለው የሚገነቡት ሞሎች በተያዘላቸው ጊዜ ይጠናቀቃሉ አሉ።
ከንቲባዋ በመሀል አራዳ እየተገነቡ ከሚገኙት ሶስት ሞሎች መካከል የአራዳ ሌግዠሪ ሞል ግንባታ የመስክ ግምገማ መደረጉን ገልጸዋል።
ከታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ ከአራዳ ፓርክ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር ተናበው እየተገነቡ ያሉት የአራዳ ሌግዠሪ ሞል፣ አዲስ ግራንድ ሞል እና ኦሊ ሞል አካባቢውን አስውበው መንፈሳችንን ሊያድሱ፣ ኢኮኖሚያችንን ሊያነቃቁ፣ ሰፊ የሥራ ዕድል ሊፈጥሩ እና ተወዳዳሪ ሊያደርጉን በፍጥነትና በጥራት እየተገነቡ ነው ብለዋል።
ሞሎቹ በከተማ አስተዳደሩ እና የግል ሴክተር አጋርነት እየተገነቡ መሆኑን ገልጸው፤ ከነዚህ ውስጥ በአይነቱ ልዩ፣ ለሀገራችን የመጀመሪያው እና ግዙፍ የሆነውን የአራዳ ሌግዠሪ ሞል ግንባታ ላይ ዛሬ የመስክ ግምገማ አድርገናል በማለት ገልጸዋል።
ግንባታው ከተጀመረ ሰባት ወራት ብቻ ማስቆጠሩን ጠቅሰው፤ ሥራው በጥራትና በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እየተከናወነ መሆኑን ተገንዝበናል ነው ያሉት።
ግንባታው ሲጠናቀቅ የከተማዋን ገቢ ለማሳደግ፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት እና ሁሉን አይነት ግብይት ከአንድ ስፍራ ለማከናወን የሚያስችል መሆኑን አመልክተዋል።
ሞሎቹ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚያሟሉት መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አብራርተዋል።
አዲስ አሰራርን በመቀበል እና አብሮ ሰርቶ ውጤታማ መሆን ይቻላል ብለው አምነው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በአጋርነት እየሰሩ ለሚገኙ የግሉ ዘርፍ አካላት ምስጋና ማቅረባቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!