አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ዞን የተጀመረውን የሻይ ቅጠል ልማት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ እየተከናወነ የሚገኘውን የሻይ ቅጠል ልማት ተመልክተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም በዞኑ የሻይ ቅጠል ልማት በጋራ የመስራት ባሕል ለልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የታየበት መሆኑን አንስተዋል፡፡
በየማሳዎቹ የአርሶ አደሮችን የመተጋገዝ ባሕል እንደተመለከቱ ጠቁመው ÷ ይህንም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በሌላ በኩል በጅማ ዞን እየተከናወነ የሚገኘው የገጠር ኮሪደር ልማት የተለያዩ የገጠር አካባቢዎችን ለማዘመን እንደሚያስችል ነው ያመላከቱት፡፡
በአብዱረህማን ሙሃመድ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!