የሀገር ውስጥ ዜና

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቀቀ

By Abiy Getahun

June 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቅቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ ፈተናውን በስኬት ለማጠናቀቅ በቅንጅት እየተሰራ ነው።

በዚህም ከክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከጸጥታ አካላት እና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የፈተና ጥያቄዎች እና የመሰረተ ልማት ዝግጅት ተጠናቅቋልም ነው ያሉት።

ኩረጃን ለማስቀረትም ፈተናዎች በከፍተኛ ስብጥር እንዲዘጋጁ መደረጉን እና ጠበቅ ያለ ቁጥጥር እንደሚኖር አስታውቀዋል።

በፈተና ወቅት ስልክን ጨምሮ ድምጽና ምስል የሚቀርጹ ኤሌክትሮኒክስ ነገሮችን መያዝ በጥብቅ መከልከሉን ጠቅሰው፤ የተከለከሉትን ነገሮች ይዘው የሚገኙ ተፈታኞች ውጤታቸው እንደሚሰረዝ አስገንዝበዋል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል።

ለፈተና ከሚቀመጡ ከ608 ሺህ ተማሪዎች ውስጥ 150 ሺህ የሚሆኑትን በበይነ መረብ ለመፈተን የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል።

በአልማዝ መኮንን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!