ስፓርት

ማንቼስተር ዩናይትድ ከአርሰናል በመጀመሪያው ሳምንት ይገናኛሉ

By Abiy Getahun

June 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2025/26 የውድድር ዓመት የጨዋታ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል።

በዚሁ መሰረት ማንቼስተር ዩናይትድን ከአርሰናል በመጀመሪያው ሳምንት የሚያገናኘው መርሐ ግብር ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል።

ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል በመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ቦርንማውዝን በአንፊልድ ያስተናግዳል።

በሌሎች የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ዎልቭስ ከማንቼስተር ሲቲ፣ ቼልሲ ከክሪስታል ፓላስ፣ አስቶን ቪላ ከኒውካስል ዩናይትድ፣ ቶተንሃም ሆትስፐር ከበርንሌይ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከብሬንትፎርድ፣ ሊድስ ዩናይትድ ከኤቨርተን፣ ብራይተን ከፉልሃም፣ ሰንደርላንድ ከዌስትሃም ዩናይትድ ይገናኛሉ።

የ2025/26 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ይጀመራል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!