የሀገር ውስጥ ዜና

ፓርቲዎችን ሕጋዊ ተፎካካሪዎች በማድረግ ዴሞክራሲያዊ ከባቢን ለመፍጠር በትኩረት ተሰርቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Melaku Gedif

June 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፓርቲዎችን ተቃዋሚ አድርጎ ከመመልከት ሕጋዊ ተፎካካሪዎች አድርጎ በማስተናገድ ዴሞክራሲያዊ ከባቢን ለመፍጠር አበክረን ሰርተናል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የፖለቲካ ምኅዳርን መክፈት በ2010 ዓ.ም የወሰንነው ቁልፍ ውሳኔ ነው ብለዋል፡፡

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ረጅም ዘመን ከኖረው ፓርቲዎችን ተቃዋሚ አድርጎ ከመመልከት ሕጋዊ ተፎካካሪዎች አድርጎ በማስተናገድ ዴሞክራሲያዊ ከባቢን ለመፍጠር አበክረን ሰርተናል ነው ያሉት፡፡

ይህ የአስተሳሰብ ሽግግር ሰላማዊ የፉክክር ባሕል ለኢትዮጵያ መፃዒ ተስፋ አስፈላጊ መሆኑን በማመን ላይ የተመሠረተ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በዚሁ አቋም ተመርተን ላለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተመዘገቡ ፓርቲዎች ጋር ተከታታይ መድረኮችን አስቀጥለን ቆይተናል ብለዋል።

ዛሬም በሰሞኑ እያከሄድናቸው ካሉ የባለድርሻ አካላት ውይይቶች አካል የሆነ ውይይት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር አካሂደናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ምክክሩ ተወካዮች ከየመጡበት አካባቢ የሚነሱ የተለያዩ ሃሳቦችን በማዳመጥ ግብዓት ለመውሰድ ያለመ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporationFacebook www.facebook.com/fanabroadcastingTelegram t.me/fanatelevisionWebsite www.fanamc.comTikTok www.tiktok.com/@fana_televisionWhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainmentFacebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporateTikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainmentAmharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!