የሀገር ውስጥ ዜና

ከወጪ ንግድ ከ7 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

By Hailemaryam Tegegn

June 19, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ከወጪ ንግድ ከ7 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተቋሙን የ11 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በዛሬው ዕለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባለፉት 11 ወራት ከወጪ ንግድ ከ7 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ መጨረሻ አጠቃላይ ገቢው ከ8 ቢሊዮን ዶላር ሊሻገር እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

ንግድን ለማዘመን፣ ሀገራዊ ገቢን ለማሳደግ፣ ህገወጥ ንግድን ለመግታት፣ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እና የገበያ መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት የተከናወኑ ተግባራትን ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡

ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ሚኒስትሩን ጨምሮ የሚኒስቴሩ የስራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

በመራኦል ከድር