ቢዝነስ

በአማራ ክልል የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ለማዘመን እየተሰራ ነው

By Yonas Getnet

June 19, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ለማሳደግና ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ፡፡

በቢሮው የግብር ትምህርትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ታዘባቸው ጣሴ እንዳሉት÷ በበጀት ዓመቱ 71 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡

ባለፉት 11 ወራት ከመደበኛና ከተማ አገልግሎት 53 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ነው ያስረዱት፡፡

በዚህም የእቅዱን 74 ነጥብ 3 በመቶ ማሳካት መቻሉን አቶ ታዘባቸው ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

የግብር አሰባሰብ ሥርዓቱን ለማዘመንና ቀልጣፋ ለማድረግ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ መከናወኑን አብራርተዋል፡፡

በክልሉ የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር እና የግብር ሥወራ ለገቢ አሰባሰብ ሒደቱ ተግዳሮት መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በሌላ በኩል ሀሰተኛ ደረሰኝ የሚያቀርቡና ያለ ደረሰኝ አገልግሎት እና እቃ የሚሸጡ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ክልሉ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ከግብር የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግና አሰባሰቡን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት፡፡

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!