የሀገር ውስጥ ዜና

በግብርና ምርት ዘርፍ የተሰጠው የደላላነት ፈቃድ ተሰረዘ

By Melaku Gedif

June 20, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በግብርና ምርቶች ዘርፍ የተሰጠው የደላላነት ፈቃድ ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል አለ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ አብዱልሃኪም ሙሉ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት ÷ በዘርፉ ምንም አይነት እሴት ሳይጨምሩ የንግድ ሥርዓቱን የሚረብሹ በርካታ ደላላዎች አሉ፡፡

ስለሆነም በእህል ምርት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በቁም እንስሳት ዘርፍ የተሰጠው የደላላነት ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን ተናግረዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ደላላዎች ከገበያው እንዲወጡ መደረጉን ጠቅሰው ÷ ከ3 ሺህ በላይ ደላሎች እና አገናኞች ርምጃ እንደተወሰደባቸውም አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በገበያው የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴዔታው፡፡

በተመሳሳይ በሲሚንቶ ገበያ ዘርፍ ነጻ የገበያ ሥርዓት በመዘርጋት የሲሚንቶ ዋጋ ከግማሽ በታች እንዲቀንስ መደረጉን አብራርተዋል፡፡

የሲሚንቶ ግብይት ሥርዓትን ሲረብሹ የነበሩ ደላላዎች ና በተለያዩ አካላት ስም ሲነግዱ የነበሩ ግለሰቦች ከዘርፉ እንዲወጡ መደረጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!