የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ማሪን ኮርፕስ ጄነራልና የአፍሪኮም አዛዥ ጋር ተወያዩ

By Hailemaryam Tegegn

June 20, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤ ምሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ማሪን ኮርፕስ ጄነራልና የአፍሪኮም አዛዥ ከሆኑት ጄነራል ማይክል ላንግሌይ ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የጋራ ፍላጎት በሆኑ የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ከጄነራል ማይክል ላንግሌይ ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል።