አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በፋፈን ዞን ቀብሪ በያህ ከተማ በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ለሚገነባው የንጽህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።
ፕሮጀክቱ በአካባቢው በስደተኛ ጣቢያ የሚገኙ 19 ሺህ ዜጎችን ጨምሮ በቀብሪ በያህና ዙሪያው የሚገኙ ከ86 ሺህ በላይ ዜጎችን ተደራሽ ማድረግ ያስችላል፡፡
አቶ ሙስጠፌ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የክልሉ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ የሕዝቡን መሰረታዊ ችግሮች የሚፈቱ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በበጀት ዓመቱ በጅግጅጋ፣ ውጫሌና ደገሃቡር ከተሞች የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡
የቀብሪህ በያ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በታቀደለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ፕሮጀክቱን በአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል፡፡
በተስፋዬ ሃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!