የሀገር ውስጥ ዜና

የዳያስፖራውን የልማት ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ ነው

By Melaku Gedif

June 20, 2025

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዳያስፖራው በልማት ሥራዎች ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት፡፡

የአገልግሎቱ የፕላን ክፍል ሃላፊ ወንድወሰን ተረፈ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የጀመረችውን ልማት ለማስቀጠል የዳስፖራው ተሳትፎ አስፈላጊ ነው፡፡

ለዚህም ዳያስፖራው በሀገር ውስጥ ልማት የሚያደርገውን ተሳትፎ ለማጠናከር እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፤ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የዳያስፖራውን ግንዛቤ የማሳደግ ሥራ መከናወኑን ጠቁመዋል።

ባለፉት 11 ወራት ከ300 ሺህ በላይ ዳያስፖራዎች በሀገር ውስጥ ልማት ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያስችል ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ ውስጥም ከ5 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑት የ2ኛ እና 3ኛ ትውልድ ወጣት ዳያስፖራዎች እንደሆኑ አንስተው ÷ በቀጣይ ወጣቶች በዲጂታል ዲፕሎማሲ ለሀገራቸው አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም 2 ሺህ 400 በላይ ለሚሆኑት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሳተፉ ምክርና ድጋፍ በመስጠት የማልማት አቅም ያላቸው እና የስራ ሀሳብ ያቀረቡ 800 ዳያስፖራዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ወደ ክልሎች መላካቸውን አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ ዳያስፖራው በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በቱሪዝምና በሌሎች ዘርፎች በመሳተፍ ለሀገር ዕድገት ሚናውን እንዲወጣ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

በሌላ በኩል ዳያስፖራው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ ለተለያዩ የልማት ሥራዎች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!