አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ሰላምን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን የህዝቡን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ ሁሉን አቀፍ የልማት ስራዎችን ለማከናወን የአመራሩ ሚና ሊጠናከር ይገባል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ።
“አርቆ ማየት አልቆ መስራት” በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ አሻጋሪ ዕድገትና የልማት ዕቅድ ላይ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ለአንድ ሳምንት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቅቋል።
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት፤ ክልሉ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም ወደ ስኬት በመቀየር ህዝቡን የልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ አመራሩ ተግቶ ሊሰራ ይገባል።
ለ25 ዓመታት የሚተገበረው የክልሉ የልማት ዕቅድ ፍኖተ ካርታ ውጤታማ እንዲሆን አመራሩ ግንባር ቀደም ሚናውን መወጣት እንዳለበት ገልጸው፤ ጥራት ያለው ዕቅድ ከማውጣት ጀምሮ ዕቅዱን ለመፈፀም ብቁ ሆኖ መገኘት ይገባል ነው ያሉት።
ሀብት በመፍጠር ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረገ ልማትን ማረጋገጥ በየደረጃው ካለው አመራር እንደሚጠበቅ አንስተዋል።
ዕቅዱ ኢትዮጵያ ከምትከተለው ብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ጋር ተጣጥሞ መዘጋጀቱን ጠቅሰው፤ በጀትን በአግባቡ ለልማት ማዋል እንደሚገባ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኃይል ከሚያባክኑ ትናንሽ ነገሮች በመውጣት በመተጋገዝ ዕቅዱን ለማሳካት ሁላችንም ግንባር ቀደም ሆነን ልንረባረብ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!