አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያ ፖሊስ ወንጀልን በመከላከል የሀገርና የሕዝብን ዘላቂ ሰላም የማስጠበቅ ተልዕኮውን በብቃት መፈጸም የሚያስችል የሰው ኃይልና ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ አቅም ገንብቷል አሉ፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ከመደበኛ ሰርተፊኬት እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።
በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ፖሊስ የሀገርን ሰላምና የዜጎችን ደህነንት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያን ሰላም በማጽናት የስልጣኔ ማዕከልነቷን ማስቀጠል ይገባል ያሉት ፕሬዝዳንቱ÷ ለዘመናት የተገነቡ መልካም ዕሴቶችን ጠብቆ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
የሕዝቡን ሰላም የሚያውኩ አካላትን ወደ ምክክር ማምጣት እንዲሁም የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ፖሊስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የወንጀል መከላከል እና ምርመራውን ለማከናወን የጀመራቸው ስራዎች የሀገርን ዘላቂ ሰላም ለማጽናት ምቹ መደላድል የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለጎረቤት ሀገራት እየሰጠ ያለው ነጻ የትምህርት ዕድል ሽብርተኝነትን እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል የተጀመረውን ጥረት እንደሚያጠናክርም ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ በርካታ የመሠረተ ልማቶች እየተገነቡ መሆናቸውን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ፤ ፖሊስ መሰረተ ልማቶችን ከኅብረተሰቡ ጋር በመጠበቅ ለረጅም ዓመት ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከተመራቂዎቹ መካከል የጎረቤት ሀገራት ተማሪዎችም ይገኙበታል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!