አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር ክልሎችን አሳታፊ ያደረገ ሥራ እየሰራሁ ነው አለ፡፡
ሚኒስቴሩ ከሁሉም ክልሎች ከተውጣጡ የሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ምክክር እያደረገ ይገኛል።
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ካይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በዘህ ወቅት እንዳሉት÷ በማህበረሰብ ተኮር የሰላም ግንባታ ውስጥ የክልሎችን ተሞክሮ ማስፋት የቀጣይ ትኩረት ነው፡፡
የሐሳብ ልዩነትን ለማጥበብ ተቀራርቦ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቀጣይነት ያለው ሰላም ለመፍጠር ሰላም ሚኒስቴር ክልሎችን አሳታፊ ያደረገ ስራ እየሰራ መሆኑን በመግለጽ ለዚህም የክልሎችን የሰላም ግንባታ ሂደቶች በየጊዜው የመገምገም ሥራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ክልሎች ሀገር በቀል የችግር መፍቻ መንገዶችን ተጠቅመው ለሰላም አስጊ የነበሩ ችግሮችን መቀነስ መቻላቸውን ተናግረዋል።
የማህበራዊ እሴቶቻችን በሀገር ግንባታ ውስጥ ሚናቸው የጎላ እየሆነ መምጣቱም በመድረኩ ተነስቷል፡፡
የክልል የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ተወካዮቹ ለሰላም አስጊ የሆኑ የግጭት ምክንያቶች በማህበረሰቡ ውይይት ዳብረው ችግሮቻቸው የሚፈቱበት መንገድ መፈጠሩን ገልጸዋል።
በቀጣይ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን በሀገር በቀል የሰላም መፍጠሪያ መንገዶች ለመፍታት አቅጣጫ ተቀምጧል።
በመድረኩ ክልሎች ከግጭት አፈታት ጋር በተገናኘ የሚተገብሯቸው መፍትሄዎች በተሞክሮነት ተነስቷል።
በአሸብር ካሳሁን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!