አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ቀጣይነት ባለው መልኩ በመተግበር ይበልጥ ማጠናከር ይገባል አሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን።
“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ የ2017 የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መደረክ ዛሬ በአሶሳ ከተማ ተካሄዷል።
በመድረኩ ላይ አቶ አሻድሊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ካለው ጠቀሜታ አኳያ ቀጣይነት ባለው መልኩ ተጠናክሮ ሊተገበር እንደሚገባ ገልጸው÷ ወጣቶች ሕብረተሰቡን በማገልገል ለሀገር ያላቸውን ፍቅር የሚገልፁበት መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል።
በአረንጓዴ አሻራ፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ደም ልገሳ እና ቤት እድሳት የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሕብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ መልካም ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ወጣቶች በክልሉ ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ወጣቶች የክረምት ወራትን ሕብረተሰቡን በማገዝ ተሳትፏቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይበልጥ እንዲለመድ እና የወጣቶች ተሳትፎ እንዲያድግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የክልሉ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ በበኩላቸው÷ በዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ100 ሺህ በላይ ወጣቶችን ተሳታፊ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል።
ከዚህ በፊት በተከናወኑ የበጎ በፈቃድ አገልግሎቶች በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የቤት እድሳት፣ ደም ልገሳ እና ሌሎች ተግባራት እንደተከናወኑ ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መድረክ ላይ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮችና ወጣቶች ተገኝተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!